በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ቦሌ ክፍለ ከተማ መቻልን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳሳሽ ሰውአገኘሁ በ39ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
ቦሌ ክፍለ ከተማ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን በማስመዝገብ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ13 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ከቀኑ 7 ሰዓት ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።