ቀጥታ፡

ፎረሙ ለከተሞች ብልጽግና እና ማንሰራራት መልካም አሻራ ጥሏል 

አዲስ አበባ፤ሕዳር 10/2018 (ኢዜአ)፡-10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ለከተሞች ብልጽግና እና ማንሰራራት መልካም አሻራ መጣሉን የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ።

10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም "የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት" በሚል መሪ ቃል በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ሲካሄድ ቆይቷል።በዛሬው እለትም የፎረሙ  የማጠቃለያ መርሀግብር ተካሂዷል።


 

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ፣የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል።

የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ በዚሁ ወቅት ፤ 10ኛው የከተሞች ፎረም የመደመር እሳቤ በተግባር የታየበት መሆኑን ተናግረዋል።

የፎረሙ ታዳሚዎች በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ስኬታማ ቆይታ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።


 

ፎረሙ ከተሞች ልምዳቸውን የተካፈሉበት አንዱ ከሌላው ትምህርት የወሰደበት መሆኑንም ተናግረዋል።

ለከተሞች ብልጽግና እና ማንሰራራት መልካም አሻራ መጣሉን ገልጸው፤ ፎረሙ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም