ቀጥታ፡

የኢትዮ-ማሌዢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ሕዳር 10/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያና ማሌዢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ ጀመረ።

በከፍተኛ የቢዝነስ ፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬን ጨምሮ የሀገራቱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣የንግድና ኢንቨስትመንት አልሚ ባለሃብቶች ተገኝተዋል።

በሀገራቱ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም ላይ የኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት ጸጋዎች አዋጭነቶችን የሚያመላክቱ የመነሻ ጽሑፎች እየቀረቡ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም