ቀጥታ፡

የማርበርግ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች

📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንድን ነው?

o የማርበርግ ቫይረስ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ነው።

o በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል።

📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ሥር ደም መፍሰስ፤

👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፤

👉 የጡንቻ እና ጀርባ ህመም፤

👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፤

👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ፤

👉 ለቫይረሱ ከተጋለጡ ከሁለት እስከ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ የበሽታው ምልክቶች ይታያሉ።

📌 የማርበርግ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው?

• በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ግንኙነት፤

• በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች፣ እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌና ሌሎች መገልገያዎች ጋር በሚኖር ንክኪ፤

• በቫይረሱ ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል።

📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶች ምንድን ናቸው?

o ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ፤

o ከታመመ ሰው ጋር ንክኪና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ተቋማት መሄድ፤

o ሞት በሚከሰትበት ወቅት አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀትና መቅበር፤ አላስፈላጊ ቀብር ሥነ-ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ።

o ከታመመ ሰው ደምና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፤

o ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእንጅ ጓንት መጠቀም።

o እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውኃ በአግባቡ መታጠብ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም