በወቅትና የአየር ሁኔታ ሳይገደብ የበርካቶች ስቃይ የሆነውን አስም እንዴት ማከም ይቻላል? - ኢዜአ አማርኛ
በወቅትና የአየር ሁኔታ ሳይገደብ የበርካቶች ስቃይ የሆነውን አስም እንዴት ማከም ይቻላል?
የድንገተኛ እና ጽኑ ህሙማን ሐኪም ዶክተር ፍጹም አሸብር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ለአስም ስለሚያጋልጡ መንስዔዎች፣ ምልክቶች፣ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄና ሕክምናው አብራርተዋል።
• የአስም ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?
የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት መጨናነቅ እና ሳል ከአስም ምልክቶች መካከል መሆናቸውን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ በአብዛኛው ምልክቶቹ በሌሊት ወይም በማለዳ እንደሚባባሱ ገልጸዋል።
• ለአስም ህመም አጋላጭ ወይም ለህመሙ መባባስ መንስዔዎቹ ምንድን ናቸው?
አለርጂዎች (የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን፣ የአየር ብክለት፣ ጭስ)፤
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣
ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ፣
ጭንቀት እንዲሁም የጄኔቲክ ቅድመ-ዝንባሌ ለአስም ህመም ከሚያጋልጡ እና ህመሙን ከሚያባብሱ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን ዶክተር ፍፁም ገልጸዋል።
• አስም ያለባቸው ሰዎች ምን ዓይነት ጥንቃቄ ያድርጉ?
ከአቧራ፣ ጭስ፣ አለርጂዎች መራቅና መጠንቀቅ፤
በኢንፍሉዌንዛ እና በኒሞኮካል ክትባቶች ወቅታዊ ክትባቶችን መውሰድ፤
በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ወቅት ሙቀት የሚሰጡ ልብሶችን መልበስ፤
ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፣
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣
የተመጣጠነ አመጋገብን ማዘውተር እና መሰል ተግባራት የአስም ህመም እንዳይባባስ ያግዛሉ ብለዋል ባለሙያው።