በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ታንዛንያ 11 ግቦችን በማስቆጠር ጅቡቲን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ታንዛንያ 11 ግቦችን በማስቆጠር ጅቡቲን አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሴካፋ ዞን ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት ጨዋታ ታንዛንያ ጅቡቲን 11 ለ 0 ረታለች።
ማምሻውን በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሉክማን አሊ ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል።
ኢሳ ቾሌ፣ ሳዳም ሃሚስ፣ ንሂንጎ ጁማ፣ ሶአን አዳም እና ዲስማስ አታናስ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ታንዛንያ በስድስት ነጥብ ምድብ ሁለትን እየመራች ነው።
የታንዛንያው ሉክማን አሊ በስድስት ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን መምራት ጀምሯል።
በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ዩጋንዳ ሱዳንን 9 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች። ቡድኑ በስድስት ነጥብ በታንዛንያ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
የምድቡ ሶስተኛ ጨዋታዎች አርብ ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄዱ ሲሆን ታንዛንያ ከዩጋንዳ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ጅቡቲ ከብሩንዲ ሌላኛው የምድቡ መርሃ ግብር ነው።
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።