ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ሰመራ-ሎጊያ ከተማ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ  

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 9/2018(ኢዜአ)፦  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ሰመራ-ሎጊያ ከተማ የልማት ስራዎችን ይመለከታሉ።  

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የምድረ ቀደምትነታችን ህያው ምስክርና የሰው ዘር መገኛ፣ የኤርታሌ እሳተ ገሞራና የዳሎል ድንቅ ገፀ ምድር ባለቤት፣ የተፈጥሮና የባህል ሀብታም ወደሆነችው የአፋሮች ውብ ከተማ ሠመራ-ሎጊያ መግባታቸውን ገልጸዋል። 


 

በሠመራ ሡልጣን ዓሊሚራህ ሐንፋሬ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ላደረጉት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለሠመራ ከተማ ነዋሪዎች ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። 


 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚመለከቱም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም