ቀጥታ፡

የአመራሩን አቅም በመገንባት የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያጠናክሩ ተግባራት ይከናወናሉ 

ሆሳዕና ፤ ሕዳር 9/2018(ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  የአመራሩን አቅም  በመገንባት የሕዝቡን  ተጠቃሚነት ይበልጥ የሚያጠናክሩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተገለጸ።

"በመደመር መንግሥት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተዘጋጀ ሁለተኛው ዙር   ስልጠና በሆሳዕና ከተማ መስጠት ተጀምሯል፡፡ 


 

በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤  ፓርቲው የአመራሩን አቅም በመገንባት የማሕበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡

ባለፉት ጊዜያት ለአመራሩ በተሰጡ ስልጠናዎች በክልሉ ዘለቂ  እድገት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል፡፡

በሁሉም መስኮች እየተመዘገቡ የሚገኙ ስኬቶችን ዘላቂ ለማድረግ አመራሩን የማብቃት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።  


 

በክልሉ የተጀመሩ የለውጡ ትሩፋቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የአመራሩን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

አመራሩ ለቀጣይ ዘጠኝ  ቀናት የሚሰጠውን ስልጠና በጥብቅ ዲሲፕሊን በመከታተል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም