ቀጥታ፡

የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና ማሌዢያ መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ ነው 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 9/2018 (ኢዜአ)፦ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም የኢትዮጵያ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና ማሌዢያ መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል።


 

የጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም ጉብኝት በኢትዮጵያ እና ማሌዢያ  መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ብልጽግና ጉዞ ውስጥም በጠቃሚ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት እንደሆነም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም