በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ከሚለማው መሬት የተሻለ ምርት ለማግኘት ታቅዷል - ኢዜአ አማርኛ
በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ከሚለማው መሬት የተሻለ ምርት ለማግኘት ታቅዷል
ጊምቢ፤ ህዳር 9/2018(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጋ መስኖ ከሚለማው ወደ 200 ሺህ ሄክታር መሬት ከሚጠጋው መሬት የተሻለ ምርት ለማግኘት መታቀዱን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።
በዞኑ የግብርና ጽህፈት ቤት የመስኖ ልማት ባለሙያ ግርማ ጃለታ፣ ዘንድሮ የተሸሻሉ የግብርና አሰራሮችን በመከተል በኩታ ገጠም ስንዴን ለማልማት ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም በበጋ መስኖ ስንዴ 196 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት 7 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ለማገኘት ታቅዷል ነው ያሉት።
በእስካሁኑ ሂደትም 75 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ጠቅሰው፤ የታቀደውን መሬት በሙሉ በዘር ለመሸፈን ርብርቡ ይቀጥላል ብለዋል።
በበጋ መስኖ የተሰማሩ አርሶ አደሮች የባለሙያ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው እስካሁንም 39ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮቹ መሰራጨቱን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ 91ሺህ አርሶ አደሮች በበጋ መስኖ ልማት እየተሳተፉ መሆኑንም አንስተዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከተሰማሩ አርሶ አደሮች መካከል ደገፋ አበራ፣ ባላቸው አነስተኛ መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴን በኩታገጠም በማልማት የተሻለ ምርት ለማገኘት ወደ መግባታቸውን ተናግረዋል።
ሌለኛው አርሶ አደር አየለ ተርፋሣ በበኩላቸው የቀረበላቸውን የግብዓት አቅርቦት ተጠቅመው የመስኖ ስንዴ እያለሙ የሚገኙ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በመኸረ እርሻው በባለሙያ ድጋፍ በመታገዝ ባገኙት መልካም ተሞክሮ የሰብል እንክብካቤውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።