በድሬዳዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ኢዜአ አማርኛ
በድሬዳዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
ድሬዳዋ፤ ህዳር 8/2018(ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ከሪማ አሊ ተናገሩ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች እና አመራሮች 20ኛውን የብሔሮች -ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በፓናል ውይይት አክብረዋል።
በመድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈጉባ ከሪማ አሊ፤ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ስናከብር በየአካባቢው ያልተገለጡ እሴቶችን በማስተዋወቅና በመጋራት እንዲሁም ለሀገር ልማትና ብልጽግና በጋራ በመትጋት መሆን አለበት ብለዋል።
ዘንድሮም ለልማት በመትጋትና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጽናት ማክበር እንዳለበት አንስተዋል።
በመሆኑም የህብረ ብሄራዊ አንድነት መገለጫና የፍቅር ምልክት በሆነችው ድሬዳዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።
የድሬዳዋ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሐይር ሐጂ ኑር፤ የበዓሉ መከበር ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጽናት የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማሳካት በጋራ ለመትጋት መሆኑን አንስተዋል።
በዚህ ረገድ በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች የላቀ ሃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸው ለውጤታማነት ቅንና ፍትሃዊ አገልጋይ በመሆን መስራት አለብን ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊ የመንግስት ሰራተኞችም በቅንነትና በታማኝነት ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ለለውጥና ማንሰራራት እንሰራለን ነው ያሉት።