የፖሊስ አባላት ሕግ የማስከበር ሚናቸውን ይበልጥ ማጠናከር አለባቸው - ኢዜአ አማርኛ
የፖሊስ አባላት ሕግ የማስከበር ሚናቸውን ይበልጥ ማጠናከር አለባቸው
ወላይታ ሶዶ፤ ሕዳር 8/2018 (ኢዜአ)፡-በክልሉ የፖሊስ አባላት የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሚናቸውን ይበልጥ ማጠናከር እንዳለባቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር ጥላሁን ከበደ አስገነዘቡ።
"ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና በሚል" መሪ ሐሳብ ለክልሉ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በስልጠናው መድረክ ባደረጉት ንግግር፤ ከኩስመና ታሪካችን ወጥተን ወደ ታደሰ ቁመና ለመሻገር የሚሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ የሚወጣ ፖሊስ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።
እንደ ሀገር የተመዘገበውን የጂኦ ስትራቴጂ አቅማችንን በማስቀጠል የክልሉና ኢትዮጵያን ሰላም ለማፅናት የፖሊስ አባላት ሕገ መንግስቱን በመጠበቅ የሕግ የበላይነት የማስከበር ሚናቸውን ይበልጥ ማጠናከር አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።