የአፋር ክልል መሶብ (ኮራ) የአንድ ማእከል አገልግሎት ስራ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የአፋር ክልል መሶብ (ኮራ) የአንድ ማእከል አገልግሎት ስራ ጀመረ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2018(ኢዜአ)፦ የአፋር ክልል መሶብ (ኮራ) የአንድ ማእከል አገልግሎት ስራ ጀምሯል።
የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ የክልሉን የመሶብ (ኮራ) የአንድ ማእከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
በመርሀ ግብሩ የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ህብረተሰቡ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም አገልግሎቶችን በቀላሉ በአንድ ቦታ የሚያገኝበት ማእከል ነው።