ቀጥታ፡

በ1ኛ ዙር የመስኖ ልማት ከ11 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአትክልትና ሥራሥር ምርት ለማግኘት እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፤ሕዳር 8 /2018 (ኢዜአ)፡- በአንደኛ ዙር የመስኖ ልማት ከ11 ነጥብ 142 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአትክልትና ሥራሥር ምርት ለማግኘት እየተሠራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።

በቢሮው የሆርቲካልቸር ሰብሎች ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ተስፋዬ ገ/ሚካኤል እንዳሉት፤ በአንደኛ ዙር የመስኖ ልማት 53 ሺህ 16 ሔክታር በማልማት 11 ሚሊየን 142 ሺህ 903 ኩንታል የአትክልትና ሥራሥር ምርት ለማግኘት ታቅዷል።


 

እስካሁን 21 ሺህ 818 ሔክታር መዘጋጀቱን ገልጸው፥ ከዚህ ውስጥ 12 ሺህ 435 ሔክታሩ በተለያዩ የአትክልትና ሥራሥር ሰብሎች ዘር መሸፈኑን አረጋግጠዋል።

በዚህ ተግባር ላይም 17 ሺህ 302 ሰዎች መሳተፋቸውን ነው ለኢዜአ የተናገሩት።

በሌላ በኩል በምርት ዘመኑ እየለማ ከሚገኘው 134 ሺህ 763 ሔክታር ፍራፍሬ 24 ሚሊየን 69 ሺህ 200 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።


 

በዚህም መሠረት እስካሁን ከ18 ሺህ 50 ሔክታር ላይ 4 ሚሊየን 142 ሺህ 950 ኩንታል የፍራፍሬ ምርት መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም