አርባምንጭ ከተማ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
አርባምንጭ ከተማ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 7 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሰረት ማቴዎስ እና መድኃኒት ዓለሙ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ወርቅነሽ መለሰ ለባህር ዳር ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል። ቡድኑ በአራት ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 12ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በአራት ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።
ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ክፍለ ከተማን 4 ለ 0 አሸንፏል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የስድስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።