ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድንን በማሸነፍ  ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 7 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ  የኢትዮጵያ መድን ተከላካይ ንጋቱ ገብረስላሴ በ18ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

በውድድር ዓመቱ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ12 ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ባለው የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።


 

በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በአምስት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ከግብጹ ፒራሚድስ በነበረበት የማጣሪያ ጨዋታ የተራዘመ መሆኑ ይታወቃል።

መድን ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታውን በቀጣይ ከሸገር ከተማ ጋር ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም