ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል  

አዲስ አበባ፤ ህዳር 7/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከልደታ ክፍለ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ። 

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች አሸንፏል። በጨዋታዎቹ 12 ጎሎችን ሲያስቆጥር የተቆጠረበት አንድ ግብ ብቻ ነው። 

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ የሆነው ንግድ ባንክ በዘጠኝ ነጥብ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በዘጠኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። 

ተጋጣሚው ልደታ ክፍለ ከተማ በውድድር ዓመቱ ካካሄዳቸው አምስት ጨዋታዎች መካከል ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ሁለት ጊዜ ሲሸነፍ በተመሳሳይ በሁለት ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል። 

ቡድኑ በአምስት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 


 

በሌላኛው መርሃ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ባህር ዳር በሊጉ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች መካከል ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ። በሶስት ጨዋታዎች ሽንፈት ሲያስተናግድ አንድ ጊዜ አቻ ወጥቷል።  ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አምስት ግቦችን አስተናግዷል። 

ቡድኑ በሶስት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። 

ተጋጣሚው አርባምንጭ ከተማ በበኩሉ እስከ አሁን  ባደረገው አራት ጨዋታ  ማሸነፍ አልቻለም። ሶስት ጊዜ ሲሸነፍ አንድ ጊዜ አቻ ወጥቷል። ቡድኑ አምስት ግብ ሲቆጠርበት ምንም ጎል አላስቆጠረም።

አርባምንጭ ከተማ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም