የከምባታ ሀምበርቾ ተራራን የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ ተችሏል - ኢዜአ አማርኛ
የከምባታ ሀምበርቾ ተራራን የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ ተችሏል
አዲስ አበባ፤ሕዳር 7/2018 (ኢዜአ)፦የከምባታ ሀምበርቾ ተራራን የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ መቻሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የሀምበርቾ ሰንሰለታማ ተራራ ላይ የታነፁት 777 ደረጃዎች እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ በተጨማሪነት የተገነቡት ዳግም 777 ደረጃዎች አካባቢውን የኢኮ ቱሪዝም ማዕከል እያደረጉት መሆኑንም ገልጿል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከምባታ ዞን ጉብኝት ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦታው በመገኘት የቱሪዝም መዳረሻው ተጨማሪ መስህቦች እንዲላበስ አቅጣጫዎችን ከሰጡ በኋላ ቦታው ትኩረት ማግኘቱንና 777 ደረጃዎች እንዲለማ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡
የሀምበርቾ 777 የኦኮ ቱርዝም ማዕከል የማህበረሰቡን የእለት ኑሮውን ሳያውክ እሴትን በመጨመር የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግን ዓላማ ያደረገ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ውጤት መታየት መጀመሩንም ገልፀዋል፡፡