ቀጥታ፡

ዩጋንዳ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ጉዞዋን ብሩንዲን በማሸነፍ ጀምራለች

አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ሁለት ጨዋታ ዩጋንዳ ብሩንዲን 4 ለ 0 አሸንፋለች።

ማምሻውን በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል በተካሄደው ጨዋታ ቶማስ ኦጌማ እና ኦዌን ሙሲካ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።

ዩጋንዳ በምድቡ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቧን አሳክታለች። 

በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ታንዛንያ ሱዳንን 6 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች። 

የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታዎች ማክሰኞ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄዱ ሲሆን ታንዛንያ ከጅቡቲ እና ሱዳን ከዩጋንዳ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም