ቀጥታ፡

ታንዛንያ ሱዳንን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈች 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታ ታንዛንያ ሱዳንን 6 ለ 0 አሸንፋለች። 

በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዲስሙስ አትሃንሲ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ንሂንጎ ሉዜሌንጋ፣ ካሲም ጁማ፣ ሶአን ሻባኒ እና ሃምሲ ባሩአ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። 

ውጤቱን ተከትሎ ታንዛንያ በሶስት ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል። 

በዚሁ ምድብ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ ብሩንዲ ከዩጋንዳ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም