ቀጥታ፡

በከተማው የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ስራዎች የዜጎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን የመለሱ ናቸው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ስራዎች የዜጎች የልማትና የመልካም አስተዳደር  ጥያቂዎችን የመለሱ መሆናቸውን የመዲናዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ህይወት ሳሙኤል ገለጹ፡፡

በተሻሻለው የፕላንኒንግ ልማት እና ተያያዥነት መመሪያ እንዲሁም ከተማዋ ላይ የሚገነቡ ህንጻዎችና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ዙሪያ መድረክ ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ህይወት ሳሙኤል በወቅቱ እንደገለጹት፤ በከተማው የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የበርካታ ዜጎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን የመለሱ ናቸው።

በኮሪደር ልማቱ የሚሰሩ መንገዶች ለእግረኞች ምቾትና የትራንስፖርት ፍሰቱ እንዲቀላጠፍ ከማድረግ አኳያ እየተጫወቱ ያለውን ሚና ለአብነት አንስተዋል።

የተሻሻለው የግንባታ ፈቃድ ከተማዋ ስሟንና ደረጃዋን ጠብቃ እንዲትሄድ ማስቻሉን አመልክተው፤ በርካታ ባለሃብቶች እና  አልሚዎች ወደ ልማት እንዲገቡ እድል መፍጠሩንም አንስተዋል።

አሁን የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥልና ተደራሽነቱን ለማስፋት የባለድርሻ አካላት ሚና ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም