ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሩዋንዳን አቻውን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ አዘጋጇ ኢትዮጵያ የሩዋንዳ አቻዋን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የምድብ አንድ በተደረገው የሁለቱ ሀገራት የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ዳዊት ካሳ እና ሁዜፋ ሻፊ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በጨዋታው ኢትዮጵያ በተጋጣሚዋ ላይ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ምድብ አንድን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች።

ቡድኑ ቀጣይ የምድብ ጨዋታውን ማክሰኞ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን አቸው ጋር ያደርጋል።

ዛሬ በምድብ አንድ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም