ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን የመክፈቻ ጨዋታ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን የመክፈቻ ጨዋታ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምታስተናግደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ዛሬ ተጀምሯል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በምድብ አንድ በተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
አናስ ሞሐመድ እና ቢላል ዩሱፍ ለሶማሊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ለደቡብ ሱዳን ሳሙኤል ዳቪድ እና ፖኖም ጁ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በምድብ አንድ የውድድሩ አዘጋጅ ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በሁለት ምድብ ተከፍሎ በሚካሄደው ውድድር 10 ሀገራት ይሳተፋሉ።
በማጣሪያው ለፍጻሜ የሚደርሱት ሁለት ሀገራት ሴካፋን ወክለው እ.አ.አ በ2026 በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ይሳተፋሉ።
የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።