ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ከሚሴን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018(ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(/) በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ከሚሴ ጉብኝት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ተገኝቼ ለሕዝቡ መልዕክት አስተላልፌያለሁ ብለዋል።


 

በአማራ ክልል ከጎበኘኋቸው ዞኖች እስከአሁን ያልጎበኘሁት ዞን በመሆኑ ጉብኝቱን የተለየ ያደርገዋል ሲሉም ገልጸዋል።

የከሚሴ የኮሪደር ልማት ሥራ በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም 1.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት እና የእግረኛ መንገድ ሥራዎች የሚመሰገኑ ናቸው ብለዋል።


 

የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝባዊ ሥፍራዎችን ደረጃ ከፍ በማድረግ ዕሳቤ በሁሉም ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተተገበረ መሆኑን ያሳያሉ ሲሉም ጠቁመዋል።

በከተማዋ ለሌማት ትሩፋት ሥራችን አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለውን የኤልፎራ አግሮ-ኢንዱስትሪ የተቀናጀ የግብርና ልማት ፋብሪካንም ጎብኝተናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም