ቀጥታ፡

የ10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ኤግዚቢሽን በሠመራ ሎጊያ ከተማ ተከፈተ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018(ኢዜአ)፦ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ 10ኛውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ኤግዚቢሽን በሠመራ ሎጊያ ከተማ አስጀምረዋል።

10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም "የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት” በሚል መሪ ሀሳብ በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡


 

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ 10ኛውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ኤግዚቢሽን አስጀምረዋል።

ኤግዚቢሽኑ ከተሞች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከተሞች ያላቸውን ምርጥ ተሞክሮ ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ መሆኑም ነው የተመላከተው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም