“ውድብ ወለዶ ትግራይ (ወለዶ)" ሕጋዊ ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
“ውድብ ወለዶ ትግራይ (ወለዶ)" ሕጋዊ ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት አገኘ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ“ውድብ ወለዶ ትግራይ (ወለዶ)" ሕጋዊ ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ሰጥቷል።
ለትግራይ ክልል አማራጭ የፖለቲካ ሃሳብ ለማቅረብ ወጣቶች የፖለቲካ ፓርቲ በመመስረት ሕጋዊ ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረባቸው ተመላክቷል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለ“ውድብ ወለዶ ትግራይ (ወለዶ)" ሕጋዊ ክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ኅዳር 05 ቀን 2018 ዓ.ም. መስጠቱን አስታውቋል።