ቀጥታ፡

የሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ የሚሆን ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 6/2018(ኢዜአ)፦ መፍጠርና መፍጠን በሚል እሳቤ የተሰራው የሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ።

አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በሆሳዕና ከተማ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም በዋና ዋና ኢኒሼቲቮች የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች በመደመር መንግሥት የተቀመጡ መፍጠርና መፍጠን የሚሉ እሳቤዎችን መሰረት ያደረጉ ናቸው ብለዋል።


 

በተለያዩ ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው በአጭር ጊዜ በሆሳዕና ከተማ የተሰራው የኮሪደር ልማት ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ መሆን የሚችል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከተሞችን ውብና ጽዱ ለማድረግ በተጀመረው እሳቤ የሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በከፍተኛ ትጋት ከተሰራ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።

በክልሉ ያሉ እምቅ የተፈጥሮ ጸጋዎችን በአግባቡ በማስተዋወቅ ክልሉን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም