በሳተላይት ችግር ምክንያት የቴሌቪዥን ስርጭት መቋረጥ አጋጥሟል - ኢዜአ አማርኛ
በሳተላይት ችግር ምክንያት የቴሌቪዥን ስርጭት መቋረጥ አጋጥሟል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 5/2018(ኢዜአ)፦የሳተላይት አቅራቢ ድርጅት በሆነው SES የቴሌ ፖርት ላይ እስራኤል አካባቢ ባጋጠመው ከፍተኛ የአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት የኃይል መቋረጥ መፈጠሩን ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡
በዚሁ ምክንያት የፋና ቴሌቪዥን እና የፋና ፕላስ እንዲሁም የአብዛኛዎቹ የሀገራችን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት ተቋርጧል፡፡
አገልግሎቱን ለመመለስ እየተሰራ በመሆኑ በትዕግስት እንዲጠብቁም ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስታውቋል።