በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ሁለተኛ ድሉን አሳክቷል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ሁለተኛ ድሉን አሳክቷል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ጨዋታ ሲዳማ ቡና አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምትኬ ብርሃኑ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥራለች።
የግቦቹ ባለቤት የሆነችው ምትኬ ብርሃኑ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በሶስት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሃዋሳ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል።