ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሃዋሳ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳግማዊት ሰለሞን በጨዋታ እና ፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ማህሌት ምትኩ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ፀሐይነሽ ጁላ እና የምስራች ላቀው ለሃዋሳ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ማህሌት ምትኩ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ድሉን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ18 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
ሃዋሳ ከተማ በ12 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን በሊጉ ከመረብ ላይ ያሳረፈቻቸውን ግቦች ወደ 11 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቷን አጠናክራለች።
በአሁኑ ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሲዳማ ቡና ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።