ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በደሴ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2018(ኢዜአ)፦  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በደሴ ከተማ የልማት ስራ ሂደትን ይመለከታሉ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአብሮነት ተምሳሌት፣ የታሪክ እና የጥበብ አምባዋ ደሴ ከተማ መግባታቸውን ገልጸዋል።  


 

በወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸው ለደሴ ከተማ ከንቲባ፣ ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለከተማው ሕዝብ ምስጋና አቅርበዋል። 


 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን የስራ ሂደት እንደሚመለከቱ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም