በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ ተግባቦት መምህሩ አንተነህ ፀጋዬ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ ተግባቦት መምህሩ አንተነህ ፀጋዬ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፤ህዳር 4/2018(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ ተግባቦት መምህር የሆኑት አንተነህ ፀጋዬ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
በዩኒቨርሲቲው ለበርካታ ዓመታት በማስተማር እና በምርምር ሥራዎች ያገለገሉት ዶ/ር አንተነህ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ኅዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ጀርመንን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ሀገራት በተለያዩ የትምህርት መስኮች እውቀት የቀሰሙት ዶ/ር አንተነህ ህይወታቸው እስካለፈበት እለት ድረስ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በብሔራዊ አጀንዳና በብሔራዊ ጥቅም ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ትንታኔዎችን ሲሰጡ የቆዩ ነበሩ።
ኢዜአ በዶ/ር አንተነህ ፀጋዬ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡