በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቱሪስት ቱንጋ እና ነጻነት መና የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ምህረት አየለ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ብቸኛውን ጎል አስቆጥራለች።
ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ቦሌ ክፍለ ከተማ አራተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ መቻል ይርጋጨፌ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።