ቀጥታ፡

አየር ኃይል የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር አኩሪ ታሪክ አለው- ሌ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 4/2018 (ኢዜአ)፡- የኢፌዴሪ አየር ኃይል የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር የአኩሪ ታሪክ ባለቤት መሆኑን የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል የተመሰረተበት 90ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።


 

ይሄንን አስመልክቶ ዛሬ በአዳማ ከተማ በተካሔደ የፓናል ውይይት ላይ ዋና አዛዡ እንደተናገሩት አየር ኃይል የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ አኩሪ ታሪክ ያለውና ብዙ ጀግኖችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም ነው።

የምሥረታ በዓሉም የአየር ኃይልን ሙሉ ዝግጁነት ብሎም የፈጠረውን ዐቅም ለማሳወቅ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።


 

በውይይቱ ላይ ዋና አዛዡን ጨምሮ የአየር ኃይል ከፍተኛ መኮንኖች የሰራዊቱ አባላት የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ እና ሌሎችም መገኘታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ለኢዜአ የላከው መረጃ ያመለክታል።

የምሥረታ በዓሉ "የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት ምልክት" በሚል መሪ ሐሳብ ደረጃውን በጠበቀ የአቪዬሽን ኤክስፖ፣ በዓይነቱ ለየት ባለ የጥቁር አንበሳ የአየር ትርዒት እና በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም