በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል ይርጋጨፌ ቡናን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል ይርጋጨፌ ቡናን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል ይርጋጨፌ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ በቂላ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ የይርጋጨፌ ቡናዋ ሰላም ፀጋዬ በ91ኛው ደቂቃ በራሷ ግብ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
የመቻሏ ሰናይት ሸጎ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ አራተኛ ድሉን ያሳካው መቻል በ13 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ይርጋጨፌ ቡና በአራት ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ሰዓት አዳማ ከተማ ከቦሌ ክፍለ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።