መቻል፣ መቀሌ 70 እንደርታ፣ ነጌሌ አርሲ እና ቦዲቲ ከተማ በኢትዮጵያ ዋንጫ ወደ ሶስተኛ ዙር አለፉ - ኢዜአ አማርኛ
መቻል፣ መቀሌ 70 እንደርታ፣ ነጌሌ አርሲ እና ቦዲቲ ከተማ በኢትዮጵያ ዋንጫ ወደ ሶስተኛ ዙር አለፉ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ጨዋታዎች ዛሬም እየተካሄዱ ነው።
በሃዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ መቻል ምድረገነት ሽሬን 3 ለ 0 አሸንፏል።
አብዱልከሪም ወርቁ በጨዋታ፣ ዮሴፍ ታረቀኝ በፍጹም ቅጣት እና የምድረገነት ሽሬው ክብሮም ብርሃነ በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በሌላኛው መርሃ ገብር ነጌሌ አርሲ ሀዲያ ሆሳዕናን በመለያት ምት 8 ለ 7 አሸንፏል። ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ሀቢብ ከማል ለነጌሌ አርሲ፣ ብሩክ በየነ ለሀዲያ ሆሳዕና ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ፋሲል ከነማን በአሸናፊ ሀፍቱ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል።
ቦዲቲ ከተማ ሃላባ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል። በጅማ ስታዲየም በተደደረገው ጨዋታ አጥናፉ ቡሸና የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።
መቻል፣ መቀሌ 70 እንደርታ፣ ነጌሌ አርሲ እና ቦዲቲ ከተማ 16ቱን ተቀላቅለዋል።
ቀሪ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ከሰዓት በኋላ ይካሄዳሉ።
ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ቤንጅ ማጂ ቡና ወደ ሶስተኛ ዙር ማለፋቸው ይታወቃል።