የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቀሪ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቀሪ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 4/2018(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ዛሬ 12 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ሀዲያ ሆሳዕና ከነጌሌ አርሲ ከረፋዱ 4 ሰዓት፣ ባህር ዳር ከተማ ከሸገር ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት እና አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ ይጫወታሉ።
ምድረገነት ሽሬ ከመቻል ከረፋዱ 4 ሰዓት፣ ሐረር ከተማ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት እና ንብ እግር ኳስ ክለብ ከየካ ክፍለ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም የሚካሄዱ ጨዋታዎች ናቸው።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መቀሌ 70 እንደርታ ከፋሲል ከነማ ከረፋዱ 4 ሰዓት፣ ድሬዳዋ ከሃዋሳ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።
ሃላባ ከተማ ከቦዲቲ ከተማ ከቀኑ 4 ሰዓት፣ ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት እና ቢሾፍቱ ከተማ ከደሴ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት በጅማ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ቤንጅ ማጂ ቡና ወደ ሶስተኛ ዙር ማለፋቸው ይታወቃል።
የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ወላይታ ድቻ በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2 ለ 0 አስተናግዶ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ተሰናብቷል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚያሸንፍ ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።