ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ የወቅቱ አሸናፊ ወላይታ ድቻ ከውድድሩ ተሰናበተ 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወላይታ ድቻን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍሬው ሰለሞን እና ጋናዊው ኮንኮኒ ሃፊዝ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ ሶስተኛ ዙር አልፏል።

በአንጻሩ የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ተሰናብቷል።

በሌላኛው መርሃ ግብር አርባምንጭ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመለያ ምት 5 ለ 4 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።

ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ በመለያየታቸው ነው ወደ መለያ ምት ያመሩት።

ቀን ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን ኢትዮ ኤሌክትሪክን፣ ቤንች ማጂ ቡና ጋሞ ጨንቻን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቅለዋል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ነገም ሲቀጥል 12 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም