ኢትዮጵያ መድን እና ቤንች ማጂ ቡና በኢትዮጵያ ዋንጫ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ መድን እና ቤንች ማጂ ቡና በኢትዮጵያ ዋንጫ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፦ የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ጀምረዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን በአማኑኤል ኤርቦ ግብ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሃ ግብር ቤንች ማጂ ቡና ጋሞ ጨንቻን 1 ለ 0 ረቷል።
ፅዮን ተስፋዬ ለቤንች ማጂ ቡና ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን እና ቤንች ማጂ ቡና በኢትዮጵያ ዋንጫ የመጨረሻውን 16 የተቀላቀሉ የመጀመሪያ ቡድኖች ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ከሰዓትም ሲቀጥል የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ወላይታ ድቻ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ አርባምንጭ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተመሳሳይ ከቀኑ 9 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።