በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባምንጭ ከተማን 5 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምርቃት ፈለቀ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ እፀገነት ግርማ፣ ንግስት በቀለ እና መሳይ ተመስገን ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል።
ድንቅነሽ በቀለ ለአርባምንጭ ከተማ ብቸኛውን ጎል አስቆጥራለች።
የንግድ ባንኳ እፀገነት ግርማ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
ንግድ ባንክ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ምክንያት ከሲዳማ ቡና እና ሸገር ከተማ ያላደረጋቸውን ተስተካካይ ጨዋታዎች በቀጣይ በሚገለጹ ቀናት የሚያደርግ ይሆናል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በአንድ ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል።
በተያያዘም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ሸገር ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።