የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ወላይታ ድቻ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ከረፋዱ 4 ሰዓት፣ አርባምንጭ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 9 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።
ቤንች ማጂ ቡና ከጋሞ ጨንቻ በሃዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ነገ በኢትዮጵያ ዋንጫ 12 ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
በመጀመሪያው ዙር ውድድር የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ብቻ የተሳተፉ ሲሆን አሸናፊ ቡድኖች በሁለተኛው ዙር ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ጋር በመቀላቀል ይጫወታሉ።
ወላይታ ድቻ የወቅቱ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ነው።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚያሸንፍ ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።