ቀጥታ፡

በተጠባቂው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ሊቨርፑልን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሊንግ ሃላንድ፣ ዠርሚ ዶኩ እና ኒኮ ጎንዛሌዝ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አርሊግ ሃላንድ በጨዋታው ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት አምክኗል።

ሲቲ በጨዋታው ከተጋጣሚው በተሻለ ለግብ የቀረቡ እድሎችን ፈጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በሊጉ ሰባተኛ ድሉን በማስመዝገብ በ22 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ ብሏል።

በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊቨርፑል በ18 ነጥብ ወደ ስምንተኛ ደረጃ ወርዷል። 

አርሊንግ ሃላንድ በሊጉ ያስቆጠረችውን ጎሎች ብዛት ወደ 12 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን አጠናክሯል።

በተያያዘም ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች አስቶንቪላ ቦርንማውዝን 4 ለ 0 ሲረታ ብሬንትፎርድ ኒውካስትል ዩናይትድን ኖቲንግሃም ፎረስት ሊድስ ዩናይትድን በተመሳሳይ 3 ለ 1 አሸንፈዋል።

ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከዓለም አቀፍ የብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ መልስ ከሁለት ሳምንት በኋላ በ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ይመለሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም