ቀጥታ፡

ማጎ ብሔራዊ ፓርክ …

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘው ማጎ ብሔራዊ ፓርክ፤ ከ20 በላይ ቀበሌዎች ያዋስኑታል።


 

ፓርኩ በአሁኑ ወቅት 1ሺህ 942 ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት እንዳለው የፓርኩ ኃላፊ አርቦር ለሌ ለኢዜአ ተናግረዋል።

በዚህ ፓርክ ውስጥም 81 አጥቢ የዱር እንስሣት እንዲሁም 237 የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉ ገልጸዋል።


 

በተጨማሪም አምሥት ዓይነት የእጽዋት ዝርያዎች መኖራቸውን ነው ያነሱት።

ፓርኩን ከሕገ-ወጥ ተግባራት ለመጠበቅ በአካባቢው ከሚገኙ የመንግሥት መዋቅሮች እንዲሁም ከኅበረተሰቡ ጋር የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።


 

በብሔራዊ ፓርኩ ከሚገኙ ዋና ዋና የዱር እንስሣት ዝርያዎች መካከል፤ ዝሆን፣ ጎሽ፣ የቆላ አጋዘን፣ የዱር አሳማ፣ መጋላ ቆርኬ፣ አንበሳ፣ ነብር፣ አቦ ሸማኔ፣ የዱር ውሻ ከፊሎቹ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም