ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 1/2018(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
አቶ ተመስገን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት የኢትዮጵያ ታሪክ አባት በመባል የሚታወቁት አንጋፋው የታሪክ ምሁርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
ፕሮፌሰር ላዺሶ በህይወት በነበሩበት ዘመን ለሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክተዋል ብለዋል፡፡
ምሁሩ የተለያዩ የታሪክ መፅሀፍትን ያሳተሙና በዘርፉ አንቱታን ያገኙ ታላቅ ሰው ነበሩ ሲሉም ገልጸዋል።
ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ተመኝዋል።