ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2018(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ. ዴሌቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለፋቸውን በታላቅ ኀዘን ሰማሁ ብለዋል።
ነፍሳቸውን በዐጸደ ገነት እንዲያኖርልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልን እመኛለሁ ሲሉም የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።