አዳማ ከተማ በሊጉ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ከተማ በሊጉ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ነቢል ኑሪ በ58ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
የኢትዮጵያ ቡናው በፍቃዱ አለማየሁ በ73ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
አዳማ ከተማ በሊጉ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በአራት ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።