ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ይርጋጨፌ ቡና ከአዳማ ከተማ ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል። 

ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ይርጋጨፌ ቡና ከአዳማ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ። 

አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በሊጉ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

አንድ ጊዜ ሲሸንፍ ሶስት ጊዜ አቻ ወጥቷል። ቡድኑ በጨዋታዎቹ ምንም ግብ አላስቆጠረም። በአንጻሩ አራት ግቦችን አስተናግዷል።

ይርጋጨፌ ቡና በሶስት በነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። 

ተጋጣሚው አዳማ ከተማ በበኩሉ እስከ አሁን በውድድር ዓመቱ ካካሄዳቸው አራት ጨዋታዎች መካከል አንዱን ሲያሸንፍ ሶስት ጊዜ ተሸንፏል። ቡድኑ አንድ ግብ ሲያስቆጥር ስምንት ግቦች ተቆጥሮበታል።

አዳማ ከተማ በተመሳሳይ ሶስት ነጥብ ባለበት የግብ እዳ ምክንያት 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

በሌላኛው መርሃ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ባህር ዳር በሊጉ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች መካከል ማሸነፍ የቻለ አንድ ጊዜ ብቻ በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች ሽንፈትን አስተናግዷል። ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አምስት ግቦችን አስተናግዷል። 

ቡድኑ በሶስት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል። 

ሲዳማ ቡና በሊጉ ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል።

አምስት ግቦችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ ሁለት ግቦች ተቆጥረውበታል። ቡድኑ በአምስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም