በፕሪሚየር ሊጉ ዌስትሃም ዩናይትድ እና ኤቨርተን ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ዌስትሃም ዩናይትድ እና ኤቨርተን ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።
ማምሻውን በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ በርንሌይን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ካሉም ዊልሰን፣ ቶማስ ሱቼክ እና ካይል ዎከርስ-ፒተርስ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ዚያን ፍሌሚንግ እና ጆሽ ኩለን ለበርንሌይ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ዌስትሃም በሊጉ ተከታታይ ድሉን ሲያስመዘግብ በአንጻሩ በርንሌይ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
በሌላኛው መርሃ ግብር ኤቨርተን ፉልሃምን 2 ለ 0 አሸንፏል። በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢድሪሳ ጌይ እና ማይክል ኪን ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኤቨርተን ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። ፉልሃም በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
መርሃ ግብሩ ምሽትም ቀጥሎ ሲውል ሰንደርላንድ ከሊጉ መሪ አርሰናል ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ30፣ ቼልሲ ከዎልቭስ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።