ድሬዳዋ በሊጉ ሶስተኛ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ድሬዳዋ በሊጉ ሶስተኛ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያሬድ ታደሰ እና አብዱልሰላም የሱፍ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ዳዊት ገብሩ ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ሶስተኛ ድሉን በማስመዝገብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአንድ ነጥብ የመጨረሻው 20ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።