ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና የሊጉ መሪ ሆነ 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና ምድረገነት ሽሬን 2 ለ 1 አሸንፏል። 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍቅረእየሱስ ተክለብርሃን እና ብርሃኑ በቀለ የማሸፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አቤል ማሙሽ ለምድረገነት ሽሬ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና በ12 ነጥብ የሊጉ መሪ ሆኗል።


 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ምድረገነት ሽሬ በአምስት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና አርባምንጭ ከተማ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ከአርባምንጭ ከተማ በኩል ይሁን እንዳሻው በ51ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። 

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በአምስት ነጥብ 10ኛ ደረጃን ሲይዝ አርባምንጭ ከተማ በሶስት ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም